ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ስለሰላም የመቁጠሪያ ጸሎት ሲያደርጉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቫቲካን ስለሰላም የመቁጠሪያ ጸሎት ሲያደርጉ   (AFP or licensors)

ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በዓለማችን ላይ የሚደረገው ጦርነት እንዲያበቃ እመቤታችንን እንማጸናት አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅድስት ሀገር፣ ዩክሬን እና ምያንማር የሚደረገው ጦርነት እንዲያበቃ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በአደራ እንዲሰጡ ለምእመናን የተማጽኖ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በተለይም በግንቦት ወር ጸሎት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዓለም ዙሪያ በጦርነት እና በግጭት ለሚሰቃዩት ብፅዕት እናታችን ማርያም  በአደራ ሰጥተው ምእመናን የመቁጠሪያ ጸሎት እንዲያደርጉ እና ይህንን ማድረግ እና መጸለይ ያለውን ትልቅ ጥቅም በድጋሚ እንዲያውቁ ጋብዘዋል።

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በተካሄደው የረቡዕ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማብቂያ ላይ ነበር ቅዱስነታቸው ይህንን ጥሪ እና ተማጽኖ ለምዕመናን ያቀረቡት።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ረቡዕ ሚያዝያ 30/2016 ዓ.ም የመቁጠሪያዋ የእመቤታችን ማርያም በዓል የሚከበርበት ቀን  አስመልክተው እና የግንቦት ወር በወር ደረጃ የማርያም ወር ተብሎ የሚጠራበት ወር በመሆኑ የተነሳ በመላው ዓለማችን ላይ ሰላም ይሰፍን ዘንድ የመቁጠሪያ ጸሎት እንዲደረግ ቅዱነታቸው የተማጽኖ ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ ቤተክርስቲያን የልመና ጸሎትን ወደ የፖፔ የመቁጠሪያ  እመቤታችን ማርያም እንደምታቀርብ ገልጿል።

ጌታ ለመላው ዓለም በተለይም ለምትወደደው እና ሰማዕት ለሆነቺው ዩክሬን እንዲሁም ለፍልስጤም ፣ ለእስራኤል እና ለሚያንማር ሰላምን እንዲሰጥ ሁሉም ምዕመን የማርያምን አማላጅነት እንዲለምን ሁሉንም እጋብዛለሁ ብለዋል።

"ጌታ ለመላው አለም በተለይም ለምትወደደው እና ለሰማዕቷ ዩክሬን እና ለፍልስጤም ፣ ለእስራኤል እና ለሚያንማር ሰላምን እንዲሰጥ ሁሉም ሰው የማርያምን አማላጅነት እንዲለምን እጋብዛለሁ"።

ቅዱስ አባታችንም ወጣቶችን፣ ሕሙማንን፣ አረጋውያንን እና አዲስ ተጋቢዎችን ለእመቤታችን አደራ ሰጥተዋል።

"በዚህ ግንቦት ወር ሁሉም ሰው ቅዱስ የሆነውን የመቁጠሪያ ጸሎት የመጸለይን አስፈላጊነት ከፍ አድርጎ እንዲመለከተው አሳስባለሁ" ብለዋል።

08 May 2024, 13:49