ፈልግ

እስራኤል በደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ በፈጸመችው የቦንብ ድብደባ የፈራረሱ ሕንጻዎች እስራኤል በደቡባዊ የጋዛ ሰርጥ በፈጸመችው የቦንብ ድብደባ የፈራረሱ ሕንጻዎች  (ANSA)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡- ሰላም የምንገነባው ነገር ነው እንጂ በኃይል የሚመጣ ነገር አይደለም አሉ!

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጣልያን ቬሮና ከተማ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ከመጀመራቸው አስቀድሞ የታተመውን "ፍትህ እና ሰላም ይተቃቀፋሉ” የተሰኘውን መጽሃፍ መቅድም ላይ ፁሑፍ ማስፈራቸው የተገለጸ ሲሆን ሁላችንም በእለታዊ ሕይወታችን ሰላምን መገንባት ይኖርብናል ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

"ሰላምን የምንገነባው እኛው ራሳችን ነን” በኃያላኑ “በምርጫ እና በአለም አቀፍ ስምምነት” ብቻ ሳይሆን “በቤታችን፣ በቤተሰባችን፣ በጎረቤታችን፣ በስራ ቦታችን፣ በምንኖርበት ሰፈራ” ሰላም መፍጠር እንችላለን ያሉት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፍትህ እና በሰላም መካከል ስላለው ግንኙነት ፅሁፎችን እና አስተያየቶችን በማሰባሰብ አዲስ መጽሐፍ በመቅድሙ ላይ አቅርበዋል።

በጣሊያነኛ ቋንቋ “La pace e la giustizia si baceranno” (“ፍትህ እና ሰላም ይተቃቀፋሉ) በሚል ርዕስ ይፋ የሆነው መጽሐፉ በቫቲካን አሳታሚ ድርጅት ታትሞ ይፋ የሆነ ሲሆን ቅዱስነታቸው በሰሜን ጣሊያን ቬሮና ከተማ ሊያደርጉት ካቀዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በፊት መጽሐፉ ረቡዕ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም በይፋ ለሽያጭ ቀርቧል።

በፍትህ እና በሰላም መካከል ያለው ጥብቅ ትስስር

“ፍትህ ከሌለ ሰላም አደጋ ላይ ይወድቃል። ሰላም ከሌለ ፍትህ ይናጋል” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጽፈዋል። "ለእግዚአብሔር እና ለሌሎች የሚገባውን የመስጠት በጎነት እንደሆነ የተረዳው ፍትህ ከሰላም ጋር በቅርበት የተሳሰረ ነው፣ በዕብራይስጡ 'ሻሎም' የሚለው ቃል እጅግ በጣም ትክክለኛ እና ተገቢ ትርጉም ያለው መሆኑ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ እውነት ነው። "ጦርነት አለመኖሩን ሳይሆን የህይወት እና የብልጽግናን ሙላት" የሚያመለክት ቃል ነው ሲሉ በጹሑፋቸው ላይ ቅዱስነታቸው አስፍረዋል።

ራስ ወዳድነት ግጭትን ይፈጥራል

"ሰላም ለፍትሃዊ ማህበረሰብ ቅድመ ሁኔታ" እንደሚሆን ሁሉ በእያንዳንዱ ግጭት "ተጎጂዎች" መካከል በመጀመርያ ደረጃ ፍትህ እንዲሰፍን ያደርጋል። ነገር ግን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት ከሆነ ሁለቱም እነዚህ ሁለት የሰው ልጅ መመዘኛዎች የሚከፍሉት “ዋጋ” አላቸው፣ “ከራስ ወዳድነት ጋር መዋጋት” ማለትም “ከእኛ” ይልቅ ‘‘የእኔን’ ማስቀደም” ነው ብለዋል።

ሁሉም ራስ ወዳድነት "ፍትሃዊ አይደለም" እና "በግል እና በማህበራዊ ህይወታችን ውስጥ ስርዓት ሲሆን ደግሞ  ለግጭት በሮች ይከፍታል፣ ምክንያቱም ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንዳሉት ከሆነ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ ተግተን እንድንሠራ ስለሚያደርገን (ወይም እንደዚህ ብለን የምንገምተውን)" እንድንፈጽም ሰልሚገፋፋን ነው ሲሉ ገልጸዋል። ጎረቤታችንን ለመጨቆን እንኳን ዝግጁ ነን፣ ጎረቤት ከመሆን የተነሳ ጠላት የሆነ፣ ስለዚህም የሚዋረድ፣ የሚደፈርስ እና የሚሸነፍ ጠላት ነው ብለዋል።

የአባ ሮማኖ ጋርዲኒ አስተምህሮ

በዚህ ረገድ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጀርመን ተወለደው ያደጉትን “ታላቅ የቬሮናዊ ዜጋ” በማያሻማ ሁኔታ የእርሳቸውን ቃል ይጠቅሳሉ፣ እርሳቸው አባ ሮማኖ ጋርዲኒ የሚባሉ ሲሆን "ነጻነት የግል ወይም የፖለቲካ ፍላጎትን በመከተል ላይ የተመረኮዘ አይደለም፣ ነገር ግን በተፈጥሮ የሚፈለገውን ነገር መከተል ማለት ነው" ማለታቸውን ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

አብ የጋርዲኒ ትምህርታዊ ተግባር እና የፍልስፍና-መንፈሳዊ ነጸብራቆች እ.አ.አ በ1930ዎቹ እና 1940ዎቹ በጀርመን “በአስፈሪው የናዚ አገዛዝ ቀንበር የተገዛች” “በተለይ በጨለማ ጊዜ ውስጥ ምልክት” ነበሩ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሙኒክ ናዚዝምን ያወገዙ አንዳንድ የኋይት ሮዝ አባላት የሆኑት ጀርመኖች ቡድን “በአባ ጋርዲኒ ፍልስፍናዊ እና ሃይማኖታዊ ጽሑፎች እንደተመሰጡ” ያስታውሳሉ። በከተማው ውስጥ ተሰራጭተው የሚገኙ ስውር በራሪ ወረቀቶችን በመጻፍ በሂትለር አምባገነናዊ አገዛዝ የሰዎችን ኅሊና ለመቀስቀስ የሞከሩት እነዚያ ወንዶችና ሴቶች ልጆች የወሰዱት የዓመፅ እርምጃ የተወሰደባቸው “ከእነዚያ ንባቦች ነው” ምርጫቸውንም ሕሊናና ነፃነት በሕይወታቸው ከፍለዋል ብሏል።

ሰላም የሚገነባው በትንንሽ ምልክቶች ቃላትና ልማዶች ነው በማለት በመጽሐፉ መግቢያ ላይ ያሰፈሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠልም “በመንገድ ላይ የሚለምን ስደተኛ በመርዳት፣ ብቻቸውን የሆኑ እና የሚያናግራቸው የሌላቸው አዛውንቶችን በመጠየቅ ሰላምን መገንባት እንችላለን። ለድሃዋ ምድራችን እንክብካቤ ማድረገ እና አክብሮት መስጠት፣ በእኛ በዝባዥ ራስ ወዳድነት  ስሜት መቀነስ ወደ ዓለም የሚመጣውን እያንዳንዱን ፅንስ መቀበል ፣ እነዚህ ምልክቶ ለቅድስት እናት ቴሬዛ እውነተኛ የሰላም ተግባር ነው ብለዋል።

“በእነዚህ ዕለታዊ እና በቀላሉ ሊገኙ በሚችሉ የሰላም እና የፍትህ ምርጫዎች፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይደመድማሉ። የአዲሱን ዓለም መጀመሪያ መዝራት እንችላለን፣ ይህም “ሞት የመጨረሻ ቃል በሌለበትና ሕይወት ለሁሉም የሚያብብበት” ነው።

 

16 May 2024, 11:00