ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ከተማ በቫቲካን አቅራቢያ በሚገኝ ቁምስና ከአረጋዊያን ካህናት ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ከተማ በቫቲካን አቅራቢያ በሚገኝ ቁምስና ከአረጋዊያን ካህናት ጋር በተገናኙበት ወቅት  

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ከተማ ከሚገኙ ከአረጋውያን ካህናት ጋር ተገናኙ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሮም ከተማ በቫቲካን አቅራቢያ በሚገኝ ቁምስና ውስጥ ከ40 ዓመታት በፊት ምስጢረ ክህነት ከተቀብሉ 70 የሚያህሉ ካህናትን አግኝተው በዝግ መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከሚከታተሉ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እና ልጆች ጋር በተገናኙበት ወቅት ሰላምታ አቅርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ማክሰኞ ግንቦት 6/2016 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ከቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ሳን ጁሴፔ አል ትሪንፋሌ በሚገኘው የሮማውያን ደብር ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን  በወቅቱ በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ቅዱስነታቸውን በጭብጨባ ተቀብለዋል።

በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በአባ ሉዊጂ ጓኔላ የተመሰረተው እና አሁንም በጓኔሊያውያን (የበጎ አድራጎት አገልጋዮች በመባልም ይታወቃል) የሚተዳደረው ቤተ ክርስቲያን፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከ40 ዓመታት በፊት ከተሾሙ 70 ከሚሆኑ ካህናት ጋር በግል የተገናኙበት ወቅት ነበር።

በሮም ከሚያገለግሉ ካህናት ጋር የተደረገ ስብሰባ

ስብሰባው ባለፈው አመት መስከረም ወር ላይ የሮማው ጳጳስ በአምስቱ የሀገረ ስብከታቸው ዘርፎች ከሰበካ ካህናት፣ ምክትል ካህናት፣ ምእመናን እና አስተዳዳሪዎች ጋር ለመገናኘት የጀመሩት ጉብኝት አካል ነው።

የመጨረሻው ስብሰባ የተካሄደው በሚያዝያ 25/2016 ዓ.ም ነበር።

15 May 2024, 11:28