ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንቺስኮስ የቫቲካን የጥንታዊ ሥነ ጽሁፍ፣ የዲፕሎማቲክ እና የአርካይቫል ጥናትና የቫቲካን የቤተ መፃህፍት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና አስተማሪዎች ጋር ር. ሊ. ጳ. ፍራንቺስኮስ የቫቲካን የጥንታዊ ሥነ ጽሁፍ፣ የዲፕሎማቲክ እና የአርካይቫል ጥናትና የቫቲካን የቤተ መፃህፍት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና አስተማሪዎች ጋር   (Vatican Media)

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ‘ዕውቀት ሁሉን አቀፍ መሆን አለበት’ አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ከሁለት ከፍተኛ የቫቲካን የትምህርት ተቋማት ውስጥ ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመገናኘት በማህበራዊ ድረ-ገጾች ውስጥ ተሸሽገው “መርዛማ፣ ጤናማ ያልሆነ እና አመፅን የሚቀሰቅስ” መረጃ በስፋት ስለሚዘዋወሩ ተማሪዎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋቸዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ሰኞ ዕለት 200 የሚደርሱ የቫቲካን የስነ ጽሁፍ፣ የዲፕሎማቲክ እና የአርካይቫል ጥናት ትምህርት ቤት 140ኛ ዓመት እንዲሁም የቫቲካን ቤተ መዛግብት ሳይንስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና መምህራን 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓላቸውን ሲያከብሩ ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሱ ተማሪዎቹን ተቀብለው ያነጋገሯቸው በክሊሜንጦስ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፥ ለሁለቱ ታዋቂ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አድናቆታቸውን ገልፀው፥ ተቋማቱ “እውነትን ለማወቅ በማንኛውም ሁኔታ ትክክለኛ ጥናትና ምርምር የሚያደርጉ ሰዎችን” የማብቃት ሥራቸው አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

“እናንተ በእውነት ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች የቀሰማችሁት ትምህርቶች በታማኝነት ለማገልገል የሚረዳ፥ በተለይ ዜናዎች አንዳንድ ጊዜ ያለ ምንም ቁጥጥር እና ምርምር በሚተላለፉበት ጊዜ ታማኝነት በጣም አስፈላጊ ግብዓት ነው” ብለዋል።

በማህበራዊ አውታረ መረቦች ውስጥ ካሉ መርዛማ መረጃዎች መጠበቅ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ተማሪዎቹ ያከናወኑትን ጠቃሚ ስኬታቸውን ገልጸው፥ በሌላ በኩል የግል እይታን ብቻ ማንፀባረቅ እንደማይገባ ከጠቆሙ በኋላ፥ “የዕውቀት ደረጃን እና ዋጋን የማሳነስ አደጋን” ጨምሮ አሁን ላለንበት ለግሎባላይዜሽን ዓለም ወሳኝ ባህላዊ ፈተናዎች ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ አሳስበው፥ ከቴክኖሎጂዎች ጋር ያለው ውስብስብ ግንኙነት እና ባህላዊ ወጎችን ጠብቆ የማቆየት ሥራ “የሌላ አካል ጫና ሳይኖርበት ሊጎለብቱ እና ሊቀርቡ ይገባል” ብለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ እና በቴክኖሎጂ እውቀት ዓለም ውስጥ ሊደበቅ ከሚችለው “መርዛማ፣ ጤናማ ያልሆነ እና አመፅ ቀስቃሽ” መረጃ መጠበቅ እንደሚገባ እና ሁሉንም ሰው ባለው ዕውቀት “ማካተት እንጂ ማግለል እንደማያስፈልግ” በድጋሚ ገልጸዋል።

ይህ አውድ፣ “ለውይይት እና ለንግግር ክፍት መሆንን፣ በተለይም የተገለሉትን እና የቁሳቁስ፣ የባህል እና የመንፈሳዊ ድህነት ያለባቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ መሆንን ይጠይቃል” ብለዋል።

“ሁሉም ጥናቶች የዛሬዎቹን ሰዎች ደካማነትና ብልጽግና የሚለኩበት እንዲሆኑ እንመኛለን! ይህ ደግሞ እናንተን ተማሪዎች ትጋት ብቻ ሳይሆን መምህራንንም ይመለከታል”

ያለፈውን መንከባከብ እና የወደፊቱን መመልከት

"ስለዚህም" ይላሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳፓሱ፥ ሁለቱ ታዋቂ የቫቲካን ትምህርት ቤቶች “ሀሳቦችን እና ልምዶችን ለመማማር እና ለመካፈል፣ በግልጽነት ለማደግ እና 'ግላዊነትን’ ለማስወገድ” ጠንክረው መቀጠል አለባቸው ካሉ በኋላ፥ ያላለፉት ዘመናት ስላከናወኑት ተግባር በክብር ወደ ኋላ ሲመለከቱ፥ “የወደፊቱን በጉጉት መጠበቅ” እና “ከባህላዊ እና ዘመናዊ ዓለም የሚመጡ ጥያቄዎችን በማስተናገድ ራሳቸውን እንደገና ለማንቃት” ድፍረት ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።

የርዕዮተ ዓለም አደጋዎች

ገና ከጅምሩ ለምርምር “በጣም ተግባራዊ እና ተጨባጭ አካሄድ” እንደነበራቸው ያስታወሱት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ፥ ሁለቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቤተ መዛግብት እና ቤተመጻሕፍት ያሏቸውን የዘመናት ቅርሶች ለአሁኑም ሆነ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ “ተጨባጭ እና ግልጽነት” የተላበሰውን መንገድን እንዲቀጥሉበት በማበረታታት ንግግራቸውን አጠናቅቀዋል።

“ከሥር መሰረታቸው በመነሳት እነዚህ ትምህርት ቤቶች አንድ ወሳኝ ባህሪ አላቸው፥ በጣም ጥሩ ተግባራዊ አቀራረብ እና ለችግሮች እና ጥናቶች ተጨባጭ አቀራረብ አላቸው፥ በተደጋጋሚ በጠቀስኩት መሰረት, ምክንያቱም ነገሮችን ካለው እውነታ ጋር ማነፃፀር ከርዕዮተ ዓለም የበለጠ ዋጋ ያለው ነገር ነው”
 
ሁለቱን ዓመታዊ ክብረ በዓሎችን ለማክበር ከካርዲናል ፓሮሊን ጋር የተደረገ ኮንፈረንስ

የቫቲካን የሥነ ጽሁፍ፣ የዲፕሎማቲክ እና የአርካይቫል ጥናቶች እና የቤተ መፃህፍት ሳይንስ ትምህርት ቤቶች እ.አ.አ. በ1884 እና 1934 በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 23ኛ እና በፒየስ 11ኛ ትዕዛዝ የተመሰረቱ ሲሆን፥ ሁለቱም በቫቲካን ሐዋርያዊ ቤተ መዛግብት እና በቫቲካን ቤተመጻሕፍት ውስጥ ይገኛሉ።

የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሮም የሚገኘው ጳጳሳዊ የሥነ ከተማ ዩኒቨርሲቲ የሚመጣው ሰኞ ከሰዓት በኋላ የእነዚህ ሁለት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ታሪካቸው የሚዳሰስበት እና የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ የሚወያይ ጉባኤ ሊያዘጋጅ እንደሆነም ተነግሯል።

በመርሃ ግብሩም ላይ ተገኝተው ንግግር ከምያደርጉ ዋና ዋና ተናጋሪዎች መካከል የቅድስት መንበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብፁዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን እና ዝግጅቱን ያዘጋጀው የቅድስት ሮማ ቤተ ክርስቲያን የቤተ መዛግብት እና የቤተ መጽሐፍት ባለሙያ የሆኑት አንጀሎ ቪንቼንዞ ዛኒ ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።
 

14 May 2024, 14:12